Ethiopique - ኢትዮጲክ
Local news and resources for Amharic speaking immigrant communities in DC-MD-VA. Web: www.ethiopique.com
- ባሳለፍነው ሰሞን ኦክቶበ 8 ከጧቱ 10፡24 ላይ አንዲት የ27 አመት ወጣት በኤ አይ በተፈጠረ ምስል በመጠቀም ለባለቤቷ አንድ ሰው ገፍትሯት ቤታቸው እንደገባ በቴክስት ትነግረዋለች። ይህንን ተከትሎም ባልየው ለፖሊስ በ911 ደውሎ ቤታቸው እየተዘረፈ እንደሆነ ይነግራቸዋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=7070
- ስምዖን ጌታቸው የተባለ የ30 ዓመት ወጣት እሁድ ኦክቶበር 12 ምሽት በሳውዝ ኢስት ዋሽንግተን ዲሲ በጥይት ተመቶ መገደሉ ቤተሰቦቹንና ማህበረሰቡን በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ የከተተ ሲሆን፤ ወዳጅ ዘመዶቹ ገዳዮቹ ወደፍትህ እንዲቀርቡና ፍርድ እንዲያገኙ እየጠየቁ ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7064
- የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS)፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው (ፎርም I-589) ሞልተው መልስ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ግለሰቦች አመታዊ የጥገኝነት ክፍያ (Asylum Fee) እንዲከፍሉ የሚያዝ ደብዳቤዎችን መላክ ጀምሯል። ዝርዝሩ ethiopique.com?p=7059
- ... ያኔ ወላጆችን ሳይ እንዲሁም አንዳንዴ ደግሞ ትልልቅ ሰዎችም ሲገቡ እስር ቤት ውስጥ የባህል አለመግባባት ይኖራል እና በጣም ያሳዝኑኝ ነበረ ። አንዴ በጣም የማይረሳኝ፦ አንድ ሰውዬ የሽንት ችግር ነበራቸው። እና በጣም ሽንት ሲያስቸግራቸው፤ ሞል ውስጥ ከመኪናቸው ጎን ወደ ዳር ሆነው ሸኑ። ሲሸኑ ያዩአቸው ነጮች ደወሉባቸው እና ታስረው መጡ። ... ዝርዝሩ ..👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=7051
- እንደ ባልቲሞር ፖሊስ መምሪያ ተጠርጣሪዎቹን የ32 ዓመቱ ኤፍሬም መለክቴ እና የ67 ዓመቷ ፋሲካ ጻዲቅ መሆናቸውን ይፋ ቢያደርግም፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በርካታ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች አሁንም ድረስ አሉ። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=7031
- በሎርተን ከተማ በተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ ምክንያት በአንድ ማይል ራዲየስ ያሉ ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ አስጠነቀቀ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7043
- በአብቹ ለማ የፌዴራል መንግስት ከተዘጋ ወደ ሁለተኛ ሳምንት ተሸጋግሯል። ቀኑ በተራዘመ ቁጥር በሠራተኞች፣ በቤተሰቦቻቸውና በአገልግሎት ሰጪ ቢዝነሶች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። ከዚህ አንፃር በቨርጂኒያ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል መለስተኛ ቅኝት አድርገናል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7026
- የትራምፕ አስተዳደር የመንግስት መዘጋቱ በዚሁ ከቀጠለምና ወደ ኖቨምበር ከተሻገረ የፉድ ስታምፕ ተጠቃሚዎችን የድጎማ ገንዘብ ለመሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ስለማይኖር ስቴቶች ለፉድ ስታምፕ ደንበኞች ገንዘብ እንዳይልኩ አስጠነቀቀ። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7020
- የፌደራል መንግስት አስረኛ ቀኑን ይዞ በቀጠለው የመንግስት መዘጋት ወቅት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ ሰራተኞችን በቋሚነት ከስራ የማሰናበት ደብዳቤዎችን (ኢሜይሎችን) መላክ ጀምሯል። ዛሬ ዓርብ ኦክቶበር 10 የፌደራል መንግስቱ የበጀትና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ረሰል ቮውት በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ “የአር.አይ.ኤፍ (RIF) ርምጃ ተጀምሯል” ሲሉ አስታውቀዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7017
- የዲስትሪክቱ የቅጥር ተሽከርካሪዎች መምሪያ (Department of For-Hire Vehicles ) በዩኒየን ስቴሽን ዙሪያ ስላሉ ህጎች ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ኦፕሬተሮች ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ኤጀንሲው እንደገለጸው፣ ደንቦቹ በከተማዋ ከሚገኙ በጣም በተጨናነቁ የትራንስፖርት ማዕከላት አንዱ በሆነው በዚህ ስፍራ የተሳፋሪዎችን፣ የአሽከርካሪዎችን እና የጎብኚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የወጡ ናቸው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7013
- አመታዊው የዩ ኤስ አርሚ የ10 ማይል ሩጫ ውድድርን በማስመልከት ዕሁድ ኦክቶበር 12 በዲሲ የሚገኙ በርካታ መንገዶች ላይ መኪና ማቆምም ሆነ ማሽከርከር እንደማይፈቀድ የዲሲ ፖሊስ አስታውቋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=7010
- የዩኤስሲአይኤስ (USCIS) ዳይሬክተር ጆሴፍ ኤድሎው የኢሚግሬሽን ማጭበርበርን እና የጥገኝነት (Asylum) ክምችትን ለመቀነስ እየሰሩ እንደሆነ አስታወቁ ዝርሩ 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6981
- በአብቹ ለማ የዋሽንግተን ፖስት የኖቨምበር 2021 ዘገባ እና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የፌቡራሪ 2025 የጥናት ውጤት በኖቨምበር 2/2021 በተካሄደው የቨርጂኒያ ምርጫ ዲሞክራቶችን ይደግፉ የነበሩ ኢትዮ-አሜሪካውያን ሳይቀሩ የሪፐብሊካኖችን ተወካይ ግሌን ያንኪንን እንደመረጡ ያመላክታል። የዚህ ገፊ ምክያንት ደግሞ በወቅቱ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተከተለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከኢትዮጵያውያንና… ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6975
- ቆይታ ከኢትዮጲክጋ – መክሊት ሀደሮ ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6983
- ማስታወቂያ ... አፍሪክጎ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያለ ለወዳጅ ዘመድ መላክ የምትፈልጉት እቃ ካለ እኛ እንላክልዎ ይሎታል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (571)-315-7834 ወይንም በ (240)-641-8828 ይደውሉ::
- በአብቹ ለማ የፌደራል መንግስት ከኦክቶበር 1/2025 እኩለ-ሌሊት ጀምሮ በከፊል መዘጋጀቱ ከታወቀ በኋላ የዲሲ ከንቲባ ብሎም የሜሪላንድና የቨርጂኒያ ገቨርነሮች የፌደራል ሠራተኞችን ለመደገፍ የተናጠልና የጋራ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ከጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ጋር በዚህ ፅሑፍ ውስጥ ተካተው ቀርበዋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6977
- Yesterday we wrapped up our final Fishing with Ethiopique of 2025. East Potomac Park was closed due to the shutdown, but we found a new spot and still had a great turnout. Thank you to everyone who joined us this season; until we meet again when the weather gets warm. #FishingWithEthiopique
- ማስታወቂያ .. ማንኛውንም እቃ ወደ ኢትዮጵያ እንልካለን + እናመጣለን ! አድራሻ 3819C S George Mason Dr, Falls Church, VA 22041 ስልክ 571-579-1286 ወይም 571-579-0939 ዋሳ ኤክስፕረስ - የልብ አድርስ
- በዚህ ፕሮግራም ላይ ታዲያ የተለመዱትን ሽልማቶች ለአሸናፊ ልጆች ያዘጋጀን ሲሆን በዚህ ወር ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው አሸናፊዎችን የ50$ ጊፍት ካርድ ሳይሆን የ100$ ጊፍት ካርድ በ3 ዘርፍ ለሚያሸንፉ ታዳጊዎች (እድሜያቸው ከ15 ያነሱ) የምንሸልም ይሆናል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6966
- የአሌክሳንድርያ ፖሊስ የ62 ዓመት አዛውንት የሆኑትን አቶ ፍቅሬን አፋልጉኝ ብሏል። ለመረጃው የዘወትር አንባቢያችንን አንተነህን dደመላሽን እናመሰግናለን። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6904
- የዋይት ኃውስ በጀት ጽህፈት ቤት ኮንግረስ እ.ኤአ ከዛሬ ከመስከረም 30/2025 ቀነ-ገደብ በፊት በጀት ማፅደቅ ካልቻለ ተጨማሪ የፌዴራል ሰራተኞች ከሥራቸው ሊባረሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6903
- ማስታወቂያ ... አፍሪክጎ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያለ ለወዳጅ ዘመድ መላክ የምትፈልጉት እቃ ካለ እኛ እንላክልዎ ይሎታል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር (571)-315-7834 ወይንም በ (240)-641-8828 ይደውሉ::
- ማስታወቂያ . . . ታዋቂዋ አርቲስት መክሊት ሀደሮ በመጪው ወር ኦክቶበር 18 2025 ላይ ከምሽቱ 8pm ጀምሮ ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው የሞንጎምሪ ኮሚውኒቲ ኮሌጅ ለ6 አመታት የለፋችበትን "ኤ ፒስ ኦፍ ኢንፊኒቲ" የተሰኘውን አልበም ታስመርቃለች። በዚህ የአልበም ምርቃት ላይ እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ይህን ሊንክ ተጭነው የመግቢያ ትኬቱን ማግነት ይችላሉ። bit.ly/meklith
- የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከኦክቶበር 1 ቀን 2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ አዳዲስ ታሪፎችን ከውጭ ኢምፖርት በሚደረጉ መድኃኒቶች፣ በከባድ መኪናዎች እና በቤት ፈርኒቸሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6889
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ መስፍን ጣሰው፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ፣ ጆ ማሞ እና ሰይፉ ፋንታሁን በዋሽንግተን ዲሲ ሊሸለሙ ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6882
- በአብቹ ለማ ለኢትዮጲክ የተዘጋጀ የሞንጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ሰርጀንት ፓትሪክ ኬፕ I-270 ሃይ ዌይ ላይ በሰዓት 110 ማይል እያሽከረከረ የነበረውን ራፋኤል ማዮርጋ የተባለ የ21 ዓመት .. ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6822
- የኢትዮጲክ ባልደረቦች ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ኦቲዝም ማህበረሰብ መስራችና ፕሬዘደንት ከወይዘሮ አዜብ አታሮ ጋር ቆይታ አድርገናል። ይከታተሉት 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6818
- ልጆችዎት ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ይማራሉ? እንግዲያውስ ይህን ያንብቡ። ኮሌጅ ፓርክ በሚገኘው የሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎችና ሰራተኞች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሰውነት (የልብስ) ቅማል መገኘቱን ተከትሎ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር አስታውቋል። ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6814
- ይህ መጠይቅ የኢትዮ-አሜሪካውያን ማህበረሰብ መሪዎቻቸውን ለመምረጥ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመሰብሰብ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በምላሾች በመንተራስ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ለመረዳትና የምናወጣቸውን መረጃዎች በአንባቢዎች ፍላጎት ለማዘጋጀት ይረዳናል። ሁሉም መልሶች ምስጢራዊነታቸው የተጠበቀ ሲሆን ምንም አይነት ማንነትዎችን የሚገልጽ መረጃ እንዳያስቀምጡ እንመክራለን። ሊንኩን ተከትለው በመሄድ መጠይቁን ይሙሉል forms.office.com/r/m4PKAxYyYj
- ከቀጣዩ ወር አንስቶ የአሜሪካ ዜግነት ለመሆን የሚፈልጉ ግሪን ካርድ ያላቸው ነዋሪዎች አዲስ እና ከቀደመው ብዛት ያለው ጥያቄዎች የሚቀርቡበት የዜግነት ፈተና እንደሚወስዱ uscis በዚህ ሳምንት ረቡዕ እ.ኤ.አ መስከረም 19/2015 ይፋ አድርጓል። የኢትዮጲክ ባልደረቦች ይህን ከግንዛቤ በማስገባት አንባቢዎች በድረ-ገጻችን ላይ የዜግነት ጥያቄዎችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲለማመዱ የሚያገለግል ጥያቄና መልስ ማቅረብ ጀምረዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6804
- የአሌክሳንድሪያ ከተማ በ811 ኖርዝ ኮለምበስ ስትሪት ላይ በሚገኘውና ዘ ዋይትሊ (The Whitley) በሚባለው አዲስ ባለ 78 ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ የሚገኙ 8 አፓርታማዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪዎች በሎተሪ ለመሸጥ ማስታወቂያ አውጥቷል። በዚህ መሰረትም አመታዊ ገቢያቸው እስከ 114,800 ዶላር ያሉ በከተማዋ የሚኖሩ ወይንም የሚሰሩ ሰዎች ማመልከት ይችላሉ ብሏል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6795
- እኛም በዘንድሮው ዝግጅት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የምትሳተፈውን ፍሬህይወት ቢረጋን አነጋግረን ነበር፣ የፌስቲቫሉን ገጽታ እና ለዝግጅቱ ያላትን ዝግጅት በተመለከተ ከኢትዮጲክጋ ያረገችውን ቆይታ እነሆ ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6785
- የዩ.ኤስ. የተወካዮች ምክር ቤት በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በታዳጊዎች የሚፈጸሙ ወንጀለኞችን አያያዝና ፍርድ በእጅጉ የሚቀይሩ በሪፐብሊካን ተወካዮች የቀረቡ ሁለት አወዛጋቢ ረቂቅ ህጎችን አጽድቋል። እነዚህ እርምጃዎች ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወንጀልን የመከላከል አጀንዳ ጋር የሚስማማና ሰፋ ያለ የሪፐብሊካን መሪዎች ግፊት ያለበት ረቂቅ ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6754
- እጬዎችን በደረጃ በመለየት የመምረጫ ዘዴ (Ranked Choice Voting) በአንድ ጊዜ ከአንድ ዕጩ በላይ ለመምረጥ የሚያስችል ዘዴ ነው። ይህ የምርጫ ዘዴ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ አውስትራሊያ፣ ኒው ዚላንድ እና ዩናይትድ ኪንግደም በመሣሠሉት ሃገራት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል። በአሜሪካ ቨርጂኒያን ጨምሮ በ28 ስቴቶች በሥራ ላይ ውሏል። በአብቹ ለማ የተዘጋጀ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6736
- ዛሬ ከሞንጎምሪ ካውንቲ ካውንስል የወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ለአምስተኛ ጊዜ የሚያካሂደው ዓመታዊ የአፍሪካ ማንነትና ቅርስ ወር ክብረ በዓል ማክሰኞ ሴፕቴምበር 16፣.. ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6741
- !!እናመሰግናለን!! We are grateful to receive this citation from the Montgomery County Council ; something we didn’t even know existed. Grateful to the Ethio-American Chamber of Commerce for advocating for us and other businesses. It’s a reminder that strong networks open doors. Thank you 🙏🏾🙏🏾
- We now have included sample US Citizenship question for our readers to test their skills. Click the link to check out the prototype. 👉🏾 ethiopique.com?p=6693
- ከአምስቱ የቨርጂኒያ የሕዝብ ት/ቤቶች መካከል በፌርፋክስና በአርሊንግተን ካውንቲዎች የሚገኙት የፌዴራል ትምህርት ዲፖርትመንትን ለትራንስጀንደር ተማሪዎች መብት ተቆርቁራችኋል በሚል ፈንድ ማገዱ አግባብነት የለውም በማለት ያቀረቡት ክስ ውድቅ ተደርጓል። በአብቹ ለማ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6693
- መልካም የኢትዮጵያ አዲስ አመት እንመኝላችኋለን! We wish you a Happy Ethiopian New Year!!
- መልዕክቱም “በፎቶግራፍ የተደገፈ የቅጣት ማስረጃ መሠረት እርስዎ በዲኤምቪ አካባቢ ሲያሽከረክሩ ከሌሎች ይልቅ ለመኪና ግጭት ተጋላጭ ነዎት። ለራስዎና ለሌሎች ደህንነት ሲሉ የፍጥነት ወሰንንና የቀይ መብራት ደንቦችን በማክበር ያሽከርክሩ።” የሚል መልዕክት ሰዷል። በአብቹ ለማ ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6694
- የዛሬ የኢትዮጲክ እንግዳችን ወይዘሮ ሳራ ናቸው። ወይዘሮ ሳራ በሶሻል ሚድያና በበርካታ መጽሀፎቻቸው ስለ ልጅ አስተዳደግና ስለ ወላጅነት ጠቃሚ መረጃዎችን ለማህበረሰባችን ያደርሳሉ። ከወይዘሮ ሳራጋ ያደረግነውን ቆይታ እነሆ ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6715
- ዛሬ ሴፕቴምበር 8 በዋለው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ በሎስ አንጀለስ በሰፊው ይከናወኑ የነበሩ የአይስ ወረራዎችንና ስደተኞችን በጅምላ የማፈስ ስራ እንዲቀጥል ፈቅዷል፡፡ ዝርዝሩ ethiopique.com?p=6684
- የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች (USCIS) ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው ደንብ መሰረት ከዚህ ቀደም ያልነበረውና የስደተኞችን ጉዳዮ ከመመርመር የዘለለ አዲስ የሕግ ማስከበር ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ዝርዝሩ 👇🏾👇🏾 ethiopique.com?p=6676
- ዛሬ ሴፕቴምበር 6, 2025፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ማይክ ጆንሰን ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ አስደንጋጭ መረጃ ለቀዋል። ለወራተ በኤፕስቲን ጉዳይ ሲብጠለጠሉ የከረሙት ፕሬዘደንት ትራምፕ ኤፍ ቢ አይ በኤፕስቲን ላይ በነበረው የወንጀል ምርመራ ወቅት በቀጥታ የኤፍ ቢ አይ ሰላይ (ጆሮ ጠቢ) እንደነበሩ ጠቁመዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6671
- በዋሽንግተን ዲሲ የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ዣኒን ፒሮ፣ የዲ.ሲ. ካውንስል የታዳጊ ወንጀለኞችን አያያዝ ላይ በጣም የላላ አሰራር እንደሚጠቀምና ይህም ወንጀለኞች የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጓል ሲሉ ክስ ካቀረቡ በኋላ ውዝግብ አስነስተዋል። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6668
- ማስታወቂያ ___ መጠይቁን ለመሙላት ይህን ይጫኑ 👉🏾 bit.ly/4genux9
- ሞንጎመሪ ካውንቲ እሁድ ሴፕቴምበር 14 2025 ቀን በዊተን ሪጅናል ፓርክ 11ኛውን ዓመታዊ የወዳጅነት ፒክኒክ ያካሂዳል። ይህ የወዳጅነት ፕሮግራም ከሁሉም ባህል፤ ዘርና የሃይማኖት አይነቶች የተውጣጡ ሰዎችን በአንድ በማገናኘት ከልዩነት ይልቅ አንድነትን ለማጠናከር የታሰበ ፕሮግራም ነው። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6661
- Reposted by Ethiopique - ኢትዮጲክLast night was a big win for @tinynewscollective.bsky.social at the @lionpubs.bsky.social awards ceremony. Members @matsusentinel.bsky.social won the best new business award and @ethiopique202.bsky.social won the public service award in the micro category.
- ይህን ደንብ ጥሰው የተገኙ አሽከርካሪዎች በአዲሱ ህግ መሰረት የ $90 ቅጣት ከመቀበላቸው በላይ በመንጃፍቃዳቸው ላይ አንድ ነጥብ ይቀጣሉ። ዝርዝሩ 👇🏾 ethiopique.com?p=6657